መጋቢዎቻችን እግዚአብሄር ይባርካችሁ

heart-body-soul-13508510የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። ዕብራውያን  13:7

ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ። ዕብራውያን  13:17

ከከፍተኛ ትምህርት እንደተመረቅሁ ተግባረዕድ  ገብቼ ለተወሰነ ጊዜ ተምሬያለሁ፡፡ በዚያ ቆይታዬ አንድ የሲቪክስ መምህር ነበረኝ፡፡ ይህ መምህር የዜግነት ትምህርት ስለሚያስተምረን ብቻ እኔ እንጨት ቆረጣና ማለስለስ ፡ ብረት መፋቅና መግጠም አይደለም የያዝኩት የሰውን አእምሮ ነው የምቀርፀው ይለን ነበር፡፡

ተመልከቱ ያ ሰው የሰውን አእምሮ በመቅረፁ እንደክብር ቆጥሮት ይመካ ነበር፡፡ ያ የእርሰሱ አስተሰሳሰብ ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ግን ስለመጋቢዎችና መንፈሳዊ አገልጋዮች ሲናገር ይባስ ብሎ ለነፍሳችሁ ይተጋሉ ይላል፡፡

መጋቢዎች የሚተጉት ስለሰዎች ንብረት አይደለም፡ ስለሰዎች ገንዘብ አይደለም ፡ ስለሰዎች ውጫዊ ውበት አይደለም፡፡ ከዚህ ሁሉ ለሚበልጥ ዘላለማዊ ለሆነ ስለ ሰዎች ነፍስ ነው የሚተጉት፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ነፍስን ከሌሎች ነገሮች ሁሉ ጋር ሲያወዳድር እንዲህ ይላል፡፡

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?ማቴዎስ 16፡26

ይህን ለነፍሳችን የመትጋትን ታላቅ ሸክም የተሸከሙትን እንዲሁም ንፁህ የክርስትና ህይወት ተምሳሌት ለመሆን ራሳቸውን የሰጡትን መጋቢዎችና መንፈሳዊያን ሁሉ እናመሰግናለን እግዚአብሄር ይባርካችሁ እንላለን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s