የልብ ጽላት

messageበየትኛውም የህይወት መሰክ ወደ ውጤት ለመድረስ እቅድ ያስፈልጋል፡፡ እቅዳችን ደግሞ ሊመዘን የሚችል እቅድ መሆን አለበት፡፡ ስንደርስበት ደረስንበርት የምንለው ስንደርስበት የምናውቀው እቅድ ያስፈልገናል፡፡ አጠቃላይ የሆነና ዝርዝር ያልሆነ እቅድ አፈፃፀሙ ሊለካ አይችልም፡፡

በክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ አገልግሎትና አገልጋይ የአገልግሎት ውጤት የሚመዘንባቸው ብዙ መንገዶች ይኖራሉ፡፡

አገልጋይ የሚመዘንበት ብዙ መንገድ ቢኖርም እንደዚህ ግን የአገልግሎት ውጤትን በግልፅ የሚያንፀባርቅ የአገልግሎት ውጤት መለኪያ መንገድ የለም፡፡

እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤ ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ። ቆላስይስ 1፡28-29

ሐዋሪያው ስለአገልግሎቱ ሲገልፅ የአገልግሎቱ ውጤት ምስክሮች ያገለገላቸው ሰዎች ህይወት መሆኑን ይናገራል፡፡ እንዳገለገልናቸው ሰዎች የህይወት ለውጥ ስለአገልግሎታችን ስለኬታማነት የሚናገርና የሚመሰክር ምንም መመዘኛ የለም፡፡

ስለ ሐዋሪያው አገልግሎት የሚናገረው በተገልጋዮቹ በልባችን የተፃፈው የክርስቶስ መልክት እንደሆነ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንፈስ የተፃፈ መልእክት የማያሻማ የአገልግሎት ውጤት ምስክር ወረቀት ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ የሚያነቡት በክርስቶስ የተለወጠ ልብ የአገልግሎታችን ውጤታማነት ማረጋገጫ ነው፡፡

እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 3:1-3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልጋይ #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

Advertisements