እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር

shephered.jpgየእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን? ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ፥ የወፈሩትን ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም። የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው። እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም። በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም። ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያሰማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልግማለሁ። እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ። ከአሕዛብም ዘንድ አወጣቸዋለሁ ከአገሮችም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በፈሳሾችም አጠገብ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።    በመልካም ማሰማርያ አሰማራቸዋለሁ ጕረኖአቸውም በረጅሞቹ በእስራኤል ተራሮች ላይ ይሆናል፤ በዚያ በመልካም ጕረኖ ውስጥ ይመሰጋሉ፥ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ ማሰማርያ ይሰማራሉ። እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፡፡ የጠፋውንም እፈልጋለሁ የባዘነውንም እመልሳለሁ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም አጠፋለሁ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተም መንጋዬ ሆይ፥ እነሆ፥ በበግና በበግ መካከል፥ በአውራ በግና በአውራ ፍየልም መካከል፥ እፈርዳለሁ። የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ በመልካሙ ማሰማርያ መሰማራታችሁ ባይበቃችሁ ነውን? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ ባይበቃችሁ ነውን? በጎቼም በእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ። ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ እነሆ፥ እኔ በወፈሩት በጎችና በከሱት በጎች መካከል እፈርዳለሁ። እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻ ስለምትገፉአቸው የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው፥ ስለዚህ መንጋዬን አድናለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ንጥቂያ አይሆኑም በበግና በበግ መካከልም እፈርዳለሁ። ሕዝቅኤል 34፡1-22

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እረኛ #መጋቢ #ፓስተር #መመገብ #መጠበቅ #ማሰማራት #መንጋ #መፈለግ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነቢያት #ነቢይ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

የልብ ጽላት

messageበየትኛውም የህይወት መሰክ ወደ ውጤት ለመድረስ እቅድ ያስፈልጋል፡፡ እቅዳችን ደግሞ ሊመዘን የሚችል እቅድ መሆን አለበት፡፡ ስንደርስበት ደረስንበርት የምንለው ስንደርስበት የምናውቀው እቅድ ያስፈልገናል፡፡ አጠቃላይ የሆነና ዝርዝር ያልሆነ እቅድ አፈፃፀሙ ሊለካ አይችልም፡፡

በክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ አገልግሎትና አገልጋይ የአገልግሎት ውጤት የሚመዘንባቸው ብዙ መንገዶች ይኖራሉ፡፡

አገልጋይ የሚመዘንበት ብዙ መንገድ ቢኖርም እንደዚህ ግን የአገልግሎት ውጤትን በግልፅ የሚያንፀባርቅ የአገልግሎት ውጤት መለኪያ መንገድ የለም፡፡

እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤ ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ። ቆላስይስ 1፡28-29

ሐዋሪያው ስለአገልግሎቱ ሲገልፅ የአገልግሎቱ ውጤት ምስክሮች ያገለገላቸው ሰዎች ህይወት መሆኑን ይናገራል፡፡ እንዳገለገልናቸው ሰዎች የህይወት ለውጥ ስለአገልግሎታችን ስለኬታማነት የሚናገርና የሚመሰክር ምንም መመዘኛ የለም፡፡

ስለ ሐዋሪያው አገልግሎት የሚናገረው በተገልጋዮቹ በልባችን የተፃፈው የክርስቶስ መልክት እንደሆነ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንፈስ የተፃፈ መልእክት የማያሻማ የአገልግሎት ውጤት ምስክር ወረቀት ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ የሚያነቡት በክርስቶስ የተለወጠ ልብ የአገልግሎታችን ውጤታማነት ማረጋገጫ ነው፡፡

እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 3:1-3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልጋይ #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

መሪዎች ያስፈልጉናል – መሪ እንሁን

n-LEADER-628x314

Children watching monsoon cloud formation

በጋራ ወደ ውጤት ለመድረስ መሪ ወሳኝ ነው፡፡ ካለ መሪ ሰዎች አንድነትም ሆነ የጋራ ቅንጅት ብሎም ወደ ውጤትና ስኬት ሊደርሱ አይችሉም፡፡

በቤተሰብና በቤተክርስቲያን የእግዚአብሄር ሰዎች ካሉበት ቦታ አግዚአብሄር ወዳየላቸው የክብር ቦታ እንዲደርሱ መሪነት አማራጭ የሌለው ፍላጎት ነው፡፡

በራእይ የሚያስተባብር መሪ በሌለበት ህዝብ መረን ይወጣል፡፡

መሪነት ደግሞ ስልጣን ወይም ማዕረግ ሳይሆን ተፅእኖ ነው ፡፡ የመሪዎች ህይወታቸው ፡ መሰጠታቸው ፡ ቅናታቸውና  ትጋታቸው በተመሪዎች ላይ ተፅእኖ ያደርጋል ሰዎችም በደስታ ይከተሏቸዋል፡፡

መሪዎች ራእይ ያላቸው መንገዱን የሚያውቁ ሌሎችን በድፍረት በመምራት ወደ ውጤትና ስኬት የሚያደርሱ ናቸው፡፡

እንደ እነዚህ አይነት መሪዎች ያስፈልጉናል፡፡ እንደ እነዚህ አይነት መሪዎች እንሁን ፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች

How I Stopped Feeling Embarrassed by My Small Church

They knew the church was small, but they came anyway. Maybe they came because it was small.

I spent too many years feeling embarrassed by my church.

Sure, there was a time when the embarrassment was well earned. For a few years, we were unhealthy, dysfunctional and hurting.

But even after we got healthy, I stayed embarrassed. Not because it wasn’t a good church or because I didn’t love the people in it.

I was embarrassed because it was small.

When new people would show up on a Sunday, I’d offer excuses. “A lot of people are gone on summer vacation today,” or “our youth group is at a convention this weekend” or “hey, it’s Arbor Day – hard to compete with that.”

They Knew It Was Small and They Came Anyway

One of the ways I learned to be okay with – and now celebrate – the value of a healthy small church, was when I started seeing it through the eyes of people who visit small churches for the first time.

The front door of a small church is not the wardrobe to the magical land of Narnia. No one expects it to magically grow huge once they step inside.

They knew it was small, but they came anyway. Maybe they came because it was small.

They aren’t anticipating world-class staging and lighting. They don’t expect the sermon to include a Hollywood-quality video segment shot by the church’s visual arts team. In fact, they may have experienced that at a big church and realized it wasn’t for them.

People who come to a small church aren’t expecting a big church experience. But they have a right to expect a really good small church experience.

People who come to a small church aren’t expecting a big church experience. But they have a right to expect a really good small church experience.

Yes, there will always be people who are surprised that a church of 50 than you do. But they’re the exception, not the rule.

Let’s Do Small Church Really Well

So, my fellow small church pastors, today I have good news and bad news (then some more good news) for all of us.

The Good News: A lot of people who come to a small church are looking for a great small church, not a scaled-down version of a big church.

The Bad News: Many of them aren’t getting the healthy, friendly small church experience they came for. (Now that’s embarrassing).

Good News: We can change the bad news.

There’s no need to be embarrassed by our small churches any more. We just need to do the small church stuff better.

Being Small Isn’t the Problem

There are many reasons some churches are unhealthy. But being small isn’t one of them.

The main reason many small churches aren’t healthy is simple. They’re not acting like a healthy small church.

The main reason many small churches aren’t healthy is simple. They’re not acting like a healthy small church.

Often, it’s because they’ve been trying to act like a big church. And that’s not healthy. Because it’s not what they are.

So let’s lay aside the unreasonable burden of trying to be like the big church we admire and become a small church to admire.

Let’s turn up the volume on what people come to a small church for:

  • Family-style friendliness
  • Access to the pastor
  • Cross-generational worship
  • A chance to learn, grow and lead
  • Personalized, relationship-based discipleship
  • To know and be known

Big churches are great at doing what big churches do.

Small churches are great at doing what small churches do.

If you’re trying to act like a big church instead of behaving like a healthy small church, you should feel embarrassed.

But if you are a healthy small church, stand tall. Even if you stay small.

source Source

መጋቢዎቻችን እግዚአብሄር ይባርካችሁ

heart-body-soul-13508510የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። ዕብራውያን  13:7

ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ። ዕብራውያን  13:17

ከከፍተኛ ትምህርት እንደተመረቅሁ ተግባረዕድ  ገብቼ ለተወሰነ ጊዜ ተምሬያለሁ፡፡ በዚያ ቆይታዬ አንድ የሲቪክስ መምህር ነበረኝ፡፡ ይህ መምህር የዜግነት ትምህርት ስለሚያስተምረን ብቻ እኔ እንጨት ቆረጣና ማለስለስ ፡ ብረት መፋቅና መግጠም አይደለም የያዝኩት የሰውን አእምሮ ነው የምቀርፀው ይለን ነበር፡፡

ተመልከቱ ያ ሰው የሰውን አእምሮ በመቅረፁ እንደክብር ቆጥሮት ይመካ ነበር፡፡ ያ የእርሰሱ አስተሰሳሰብ ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ግን ስለመጋቢዎችና መንፈሳዊ አገልጋዮች ሲናገር ይባስ ብሎ ለነፍሳችሁ ይተጋሉ ይላል፡፡

መጋቢዎች የሚተጉት ስለሰዎች ንብረት አይደለም፡ ስለሰዎች ገንዘብ አይደለም ፡ ስለሰዎች ውጫዊ ውበት አይደለም፡፡ ከዚህ ሁሉ ለሚበልጥ ዘላለማዊ ለሆነ ስለ ሰዎች ነፍስ ነው የሚተጉት፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ነፍስን ከሌሎች ነገሮች ሁሉ ጋር ሲያወዳድር እንዲህ ይላል፡፡

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?ማቴዎስ 16፡26

ይህን ለነፍሳችን የመትጋትን ታላቅ ሸክም የተሸከሙትን እንዲሁም ንፁህ የክርስትና ህይወት ተምሳሌት ለመሆን ራሳቸውን የሰጡትን መጋቢዎችና መንፈሳዊያን ሁሉ እናመሰግናለን እግዚአብሄር ይባርካችሁ እንላለን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes